Trade Competition and Consumer Protection Draft Regulation : Drafted by the Ethiopian Trade Competition and Consumer Protection Authority

Trade Competition and Consumer Protection Draft Regulation : Drafted by the Ethiopian Trade Competition and Consumer Protection Authority

 

 

በኢፌዴሪ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን

 

 

 

 

የውህደት መመሪያ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጥቅምት 2008

 

 

 

 

 


                                    መመሪያ ቁጥር——/2008

  

የንግድ ሥራ ሀገሪቱ በምትከተለው የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መርህ መሰረት ተገቢውን ስርዓት ተከትሎ መሄድ ያለበት በመሆኑ፤

በነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የኢኮኖሚ ልማትን ለማፈጠን፤ የሸማቾችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እና የንግዱን ማህበረሰብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስለሆነ፤

ቁጥጥር የማይደረግበት ውህደት የንግዱ ውድድሩን፤ የህዝብ ጥቅም እና ገበያውን የሚያዘባና የሚጎዳ በመሆኑ፤

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ውህደትን ለመቆጣጠር በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣን   ለመወጣት የሚያስችል መመሪያ ባለመኖሩ ምክንያት በአፈጻጸም እና በአሰራር ላይ ክፍተት በመፈጠሩ፤ የውህደት ተግባራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤

ይህ መመሪያ በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 46(2) መሰረት ተደንግጎዋል፡፡

ክፍል አንድ

  ጠቅላላ

 1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የውህደት መመሪያ ቁጥር…../2008 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 1. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፤

 • ባለሥልጣን ማለት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ነው
 • ዋና ዳይሬክተር ማለት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር ነው፡፡
 • ምክትል ዋና ዳይሬክተር ማለት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ውህደት ዳይሬክቶሬት የሚገኝበት ዘርፍ የሚመራ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ማለት ነው
 • ዳይሬክተር ማለት የኢ.ፌ.ድ.ሪ በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የውህደት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ነው
 • የንግድ ስራ ማለት የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 2 (6) የተሰጠው ትርጓሜ ማለት ነው፤
 • አዋጅ ማለት የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ማለት ነው
 • የንግድ ማህበራት ማለት በንግድ ህግ አንቀጽ 210 የተሰጠው ትርጋሜ ማለት ነው
 • ነጋዴ ማለት በአዋጁ አንቀጽ 2 (5) የተሰጠው ትርጓሜ ማለት ነው፡፡
 • የንግድ መደብር ማለት በንግድ ህግ አንቀጽ 124 የተሰጠው ትርጋሜ ማለት ነው
 • የውህደት ማስታወቂያ ማለት ለመዋሀድ ዕቅድ ያላቸው ወገኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የሚያቀርቡት ማመልከቻ ማለት ነው፡፡
 • የውህደት ዳሰሳ ጥናት ማለት ውህደት ለመፍቀድ ወይም ለመከልከል ወይም ለመሰረዝ በንግድ ውድድሩ ላይ ያስከተለውን ወይም ሊያስከትል የሚችለውን የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው ወይም እንደሌለው ለማጣራት የሚከናወን ተግባር ነው፡፡

 

ይህ መመሪያ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፤

 • ውህደት በንግድ ውድድር፤ በገበያ እና በህዝብ ጥቅም ላይ የሚያስከትለውን የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ መከላከል፤
 • በአዋጁ መሰረት የሚታዩ የውህደት ደርጊቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት
 1. የተፈጻሚነት ወሰን

የዚህ መመሪያ ወሰን በአዋጁ አንቀፅ 4 የተቀመጠው የተፈጻሚነት ወሰን ነው፡፡

 

 

ክፍል ሁለት

ውህደትን የሚከታተሉ አካላት ስልጣን ተግባር፤የውህደት ትርጉም

 1. የዋና ዳይሬክተር ስልጣን
  • የውህደት ጉዳዮችን በተመለከተ ስራዎችን በበላይነት ይመራል፤
  • በዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በኩል የሚቀርቡለትን የውሳኔ ሀሳቦች ወድያው ይመለከታል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል ወይም ይወስናል፡፡

 

 1. የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ስልጣንና ተግባር
  • ከውህደት ዳይሬክቶሬት ስራዎችን ይከታተላል ድጋፍ ይሰጣል፡፡
  • ዋና ዳይሬክተሩ ውህደትን በተመለከተ ያሉትን ስልጣንና ተግባሩን በከፊል ወይም በሙሉ በውክልና የሚሰጠውን ያከናውናል፡፡
  • ከውህደት ዳይሬክቶሬት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳቦች በመመርመርና በማረጋገጥ እንዳስፈላጊነቱ የራሱን ሃሳብ በማከል ለዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፡፡

 

 1. የውህደት ዳይሬክተር ስልጣን
  • የውህደት ዳይሬክቶሬት ስራዎችን ያቅዳል ይመራል፡ይቆጣጠራል ያስተባብራል፡፡
  • የውህደት ማስታወቂያ በመቀበል አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች መያዛቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • የውህደት ዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ጥናቱ በበቂ ትንታኔ የታገዘ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በዚህ አግባብ የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ ለዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፡፡
  • እንዳስፈላጊነቱ የውህደት ተሳታፊ ወገኖች ተጨማሪ መረጃ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል፡፡
  • የውህደት ጉዳዮችን በተመለከተ አስፈላጊ መረጃዎች ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲያዙ ያደርጋል፤ያደራጃል፡፡
  • ዋና ዳይሬክተሩ የውህደት ጉዳዮችን በተመለከተ ለስራው ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ስልጣንና ተግባሩን በከፊል ወይም በሙሉ በውክልና ለውህደት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሚሰጠውን ያከናውናል፡፡

 

 

 

 1. የውህደት ትርጉም

ውህደት ማለት በአዋጁ አንቀጽ 9(3) እንደተደነገገው ግላዊ ተቋምነታቸውን ይዘው ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ የንግድ ማህበራት ሲቀላቀሉ ወይም አንድ ዓላማ ያለው የንግድ ስራ ለማከናወን ሁሉንም ወይም ከፊሉን ሀብታቸውን ሲያቀላቅሉ ወይም በአንድ ሰው ወይም በብዙ ሰዎች በግዥ ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ሁኔታ የንግድ ማህበር አክስዮኖች፤ ሴኩሪቲዎች ወይም ንብረቶች የራስ ሲደረጉ ወይም የሌላ ሰው የንግድ መደብርን አመራር መቆጣጠር ሲቻል፤ የውህደት ድርጊት እንደተፈጸም ይቆጠራል፡፡

 1. የውህደት ዓይነቶች

9.1. ለዚሀ መመሪያ አፈጻጸም የንግድ  የኢኮኖሚ  ሰንሰለትን መሰረት  በማድረግ የውህደት

ዓይነቶች የጎንዮሽ ዉህደት፤ከላይ ወደታች ዉህደት እና ጥርቅምቅም ዉህደት  በማለት

ይከፈላሉ፡፡

ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም ሲባል፡

. የጎንዮሽ ውህደት ማለት በተመሳሳይ የገበያ እና መልክዓ ምድራዊ ክልል ዉስጥ በሚገኙ

   ተወዳዳሪ በሆኑ ወይም ሊሆኑ በሚችሉ በተመሳሳይ የማምረት ወይምየማከፋፈል ሰንሰለት

ውስጥ በሚገኙ ተወዳዳሪዎች መካከል የሚፈጠር የዉህደት አይነት ነው፡፡

. ከላይ ወደታች ውህደት ማለት በተለያየ ደረጃ የሚሰሩ ነጋዴዎች ሆነው ነገር ግን አንዱ

    ለአንዱ ማሟያ ደረጃ ላይ የሚገኝ የምርት ሂደት ሰንሰለት ዉስጥ በሚገኙ መካከል የሚደረግ

ውህደት ነው፡፡

 . ጥርቅምቅም ውህደት ማለት የተለያዩ የገበያ ምርትና  አገልግሎት ውስጥ  ባሉ አቅራቢዎች

    መካከል የሚደረግ ውህደት ነው፡፡የተለያዩ ነገር ግን ግንኙነት ያላቸው ምርቶችን በሚያመርቱ

ድርጅቶች መካከል የሚፈጠር ውህደት እና  የማይገናኙ  ምርቶችን  በሚያመርቱ ድርጅቶች

መካከል የሚፈጠር ውህደቶች በዚህ የውህደት ዓይነት ውስጥ ይካተታሉ፡፡

 

 1. ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም ሲባል የንግድ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወይም ግለሰቦች የሚፈጽሙትን የግብይት ዓይነት መሰረት በማድረግ ውህደት የአክሲዮን ባለቤትነት ፤የሀብት ባለቤትነት የድርጅቶች ጥምረት የሴኩሪቱ ባለቤትነት በመባል በአራት ይከፈላል፡፡

 

ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም ሲባል፡-

. የአክስዮን ባለቤትነትን ማለት ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ግላዊ ተቋምነት ካላቸው ከራስ

   ወይም ሌሎች ድርጅቶች  አክሲዮን በግዢ  ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ የአክሲዮን

ባለቤትነት ሲኖራቸው ነው፡

 

. የሀብት ባለቤትነት ማለት ድርጅቶች ወይም ግለሰቦቸ ያላቸውን አንድ የተወሰነ ሃብት

   ለሌላ ድርጅት በሽያጭ ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ ሲያስተላልፉ ነው፡፡

 

. የድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ጥምረትማለት የንግድ ማህበራት ወይም ግለሰቦች አንድ

    ዓላማ ያለው የንግድ ስራ ለማከናወን ሁሉንም  ወይም ከፊሉን  ሀብታቸውን ሲያቀላቅሉ

የሚፈጥሩት ጥምረት ማለት ነው፡፡

 

. የሴኩሪቲ ማለት፡- ገንዘብ ነክ ያላቸው ሰነዶች ሆነው በግዢ ወይም በሌላ በማናቸውም

    መንገድ የሚተላለፍ ሰነድ ነው፡፡

ከላይ በአንቀጽ 10 ስር የተዘረዘሩት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ተቆጣጥሮ መያዝ፤ዓመታዊ የሽያጭ/ ሃብት፤ የገበያ ድርሻ ፤በገበያ ውስጥ የአቅራቢዎች ስብስብ መጠን እና አግባብነት ያለው ገበያ በውህደት ዳሰሳ ወቅት ከግምት ውስጥ የሚገቡ ይሆናሉ፡፡

. ተቆጣጥሮ መያዝ ማለት አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ የሌላዉን ድርጅት ወይም ግለሰብ

   ከ50% በላይ ድርሻ ሲይዝ ወይም በጠቅላላ ጉባኤ  አብላጫ ድምፅ  መስጠት ሲችል ወይም

የቦርድ አባላትን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በአብላጫ ድምፅ መምረጥ የሚችልበትን ወይም

ውሳኔያቸዉን በድምፅ መሻር የሚችልበትን ሁኔታ የሚፈጥር ወይም የድርጅቱን ፖሊሲ ላይ

ተፅእኖ ማሳደር የሚችልበትን ሁኔታ የሚፈጥር ከሆነ ነው፡፡

 

. ዓመታዊ የሽያጭ ገቢ ማለት ከማንኛውም የንግድ እቃ ወይም አገልግሎት ሽያጭ የተገኘ

   ውሳኔ ከሚሰጥበት አመት በፊት የነበረ የመጨረሻ አመት አጠቃላይ የሽያጭ ገቢ ሲሆን፤

የንግድ  ድርጅቱ አዲስ  ከሆነ እና  የስራ  ዘመኑ ከአንድ የበጀት አመት  በታች  ከሆነ

በሰራባቸው ጊዜያት የተገኘ አጠቃላይ ገቢ ሆኖ ህጋዊ ፈቃድ ባለው የሂሳብ ወይም የኦዲተር

ባለሙያ የተረጋገጠ ሰነድ ነው፡፡

 

. የገበያ ድርሻ ማለት አግባብነት ባለው የገበያ ወይም የምርት ክልል ውስጥ አንድ ድርጅት

   ወይም ግለሰብ  የምርት ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ገቢን ወይም  አቅምን  ወይም የምርት

ብዛትን  መሰረት ያለው የገበያ ድርሻ የሚያሳይ ነው፡፡ የገበያ ድርሻ ለማስላትም የምርት ሽያጭ መጠን ለአጠቃላይ በገበያው ውስጥ ያሉ የሌሎች ድርጅቶች የሽያጭ መጠንን በማካፈል ይሰላል፡፡

 

. በገበያ ውስጥ የአቅራቢዎች ስብስብ መጠን   ማለት  የአቅራቢዎች   ስብስብ መጠን

አግባብነት ባለው የገበያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው አቅራቢዎች ምን ያህል

እንደሆኑና እነዚህ አቅራቢዎች  ከአጠቃላይ  ገበያው ወይም ኢንዱስትሪው ውስጥ ምን ያህል

ድርሻ እንዳላቸው ለማየት የሚረዳ ነው፡፡ ይህንን ለመለካት የሚውሉ ዘዴዎች በአባሪ ቁጥር..

የሚገኘው ነው፡፡

 

. አግባብነት ያለውን ገበያ  ማለት የምርት ወይም አገልግሎት እና ምርቱ የሚገኝበት

   አካባቢን የሚያካትት ሲሆን በውድድር ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ ለመዳሰስ ይረዳል፡፡

ክፍል ሶስት

የውህደት ማስታወቂያ  ስለማቅረብ

 1. ማንኛም ነጋዴ በውህደት ስምምነት ወይም ቅንብር ውስጥ ለመሳተፍ ሲያቅዱ የውህደት ማስታወቂያ በጽሁፍ ሆኖ በአመልካቾች በራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሊቀርብ ይችላል፡፡
 2.  የማቅረቢያ  ቋንቋ እና መንገዶች
  • የውህደት አመልካቾች ማስታወቂያቸውን ለባለስልጣኑ በአካል ወይም  በፋክስ ወይም በኢሜል ወይም በፖስታ አመልካቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ማመልከቻቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡  
  • . አመልካቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የውህደት ማመልከቻቸውን እና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን በአማርኛ ቋንቋ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ የተዘጋጁ ሰነዶች ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉመው መቅረብ አለባቸው፡፡

 

 

 

 

 1. የውህደት ማስታወቂያ ይዘት እና ቅድመ ሆኔታዎች

13.1 የውህደት ማስታወቂያ የሚከተሉትን ይዘቶች ያካተተ መሆን አለበት እነሱም፤

ቀን፤የተዋሀጆች ስምና አድራሻ ፤የንግድ ስራ ቦታ፤ ያቀዱት የንግድ ስራ፤የውህደት ሁኔታ፤

የካፒታል መጠን ፤የማስረጃዎች ዝርዝር የአመልካቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ፊርማ እና

ማህተም ናቸው፡፡

 

 • የውህደት አመልካቾች የንግድ ማህበራት በሆኑ ጊዜ የታደሰ የንግድ ፈቃድ/ምዝገባ ፣ህጋዊ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ ድርጅቶች መወሃድ ስለመፈለጋቸው የሚገልጽ ተመላሽ ኦሪጅናል ወይም የተረጋገጥ ኦሪጅናል ኮፒ ቃለ ጉባኤ፣በሚሞላው ቅጽ ላይ የሚያርፍ የሚወሃዱት ድርጅቶች ማህተም ፣ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ለውጭ አገር ድርጅቶች ወይም ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በጋራ በሚሰሩ የውጪ ዜጎች  ከሆነ በወቅቱ ስራ ላይ ባለው የኢንቨስትመንት አዋጅ በተቀመጠው መስፈርት፤ በውጭ ድርጅቶች የሚቀርቡ ሰነዶችና ማስረጃዎች እንደ አግባብነቱ በንግድ ሚኒስቴር፤ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር፤ በሂሳብ አዋቂ ወይም ኦዲተር የተረጋገጠ የኦዲት ሰነድ፤ ወይም በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተረጋገጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችና ማስረጃዎች መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

 

 • የውህደት አመልካቾች ግለሰቦች ሆነው የአክሲዮን፣ ሴኩሪቲ ከንግድ ድርጅቶች ለመግዛት   በሆነ ጊዜ ግለሰቡን የሚገልጽ የታደሰ የመኖሪያ መታወቂያ፤ፓስፖርት መግዛት የሚፈልገው የአክሲዮን፤ ንብረቶች ወይም ሴኩሪቲ መጠን በብር (በቃለ ጉባኤ ወይም በደብዳቤ የተደገፈ)፣ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ፣ ለውጭ አገር አመልካች ከሆነ በወቅቱ ስራ ላይ ባለው የኢንቨስትመንት አዋጅ በተቀመጠው መስፈርት፡ ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችና ማስረጃዎች መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

 

 

 

 

 

ክፍል አራት

                                      የውህደት ዝቅተኛ ገደብ በጠቅላላው

 1. የውህደት ዝቅተኛ ገደብ
  • ዝቅተኛ ገደብ ማለት በንግድ ውድድር፤ በገበያ እና በህዝብ ጥቅም ላይ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖራቸው የሚችሉ የውህደት አይነቶች ለመለየት የሚያስችል ዝቅተኛ ገደብ ነው፡፡
  • ባለስልጣን መ/ቤቱ ውህደትን በሚመረምርበት ወቅት ዝቅተኛ ገደብን ለመወሰን የአመልካቾችን አመታዊ ሽያጭ፤ንብረት ወይም ያስመዘገቡትን ካፒታል ድምር መነሻ ሊያደርግ ይችላል፡፡
  • አመልካቾች ስለሚኖራቸው መነሻ ካፒታል በሌላ ህግ የተወሰነ ከሆነ በህጉ ላይ
  • የተቀመጠው የካፒታል መጠን የዝቅተኛ ገደብ መነሻ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 2. በዚህ ደንብ ውህደትን ለመቆጣጠር አላማ ውህደት ቀላል፤ መካከለኛ እና ከፍተኛ ተብሎ

ሊመደብ ይችላል፡፡

 1. ዓመታዊ  ሽያጭ፤ ንብረት ወይም ያስመዘገቡትን ካፒታል መጠናቸው ከ30,000,000.00 (ሰላሳ  ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር በታች ቀላል ውህደት በሚል የሚመደብ ሲሆን የካፒታል መጠናቸው ከ30,000,000.00 (ሰላሳ ሚሊዮን ) እስከ 300,000,000.00 (ሶስት መቶ ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር መካከለኛ ውህደት እንዲሁም ከ300,000,000.00 (ሶስት መቶ ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር በላይ ያለው ውህደት ከፍተኛ ተብሎ ይወሰዳል፡፡
 2. ከዚህ በላይ በአንቀጽ 20 የተቀመጠ አመታዊ ሽያጭ፤ንብረት ወይም ያስመዘገቡትን ካፒታል መጠን ዝቅተኛ ገደብ መነሻው የውህደት አመልካቾች አመታዊ ሽያጭ፤ንብረት ወይም ያስመዘገቡትን ካፒታል መጠን ድምር ነው፡፡
 3. ከዝቅተኛ ገደብ በላይ የሆኑ የውህደት አመልካቾች ለመዋሀድ ሲያቅዱ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ አለባቸው የዳሰሳ ጥናትም ይደረግባቸዋል፡፡
 4. አመታዊ ሽያጭ፤ ንብረት ወይም ያስመዘገቡትን ካፒታል መጠናቸው ከ30,000,000.00 (ሰላሳ ሚሊዮን) የኢትዮጵያ ብር በታች የሆኑ የውህደት ማስታወቂያዎች በተመለከተ ተዋሀጆች ባለስልጣኑን እንዲያሳውቁ በአዋጁ ቢቀመጥም ለባለስልጣኑ እንዳሳወቁ ተቆጥሮ ባሉበት የውህደት ፈቃድ ለመመዝገብ ስልጣን ላለው አካል ማሳወቅ አለባቸውም፡፡ ለዝቅተኛ ውህደት ማስታወቂያዎች  የዳሰሳ ጥናት ስራዎች አይካሄድባቸውም፡፡ ነገር ግን ባለስልጣን መ/ቤቱ ውህደቱ በገበያ ላይ ያለውን ተጽእኖ ከመከታተል እና ከማጣራት አያግደውም፡፡
 5. የውህደቱ ማስታወቂያው የንግድ መደብር አመራርን መቆጣጠር የሚመለከት ሲሆንና የአመራር ቁጥጥሩ የንግድ መደብሩን የአክሲዮን ግዥ እና ማስተላለፍን 50 ፐርሰንት እና ከዚያ በላይ ሲሆን ከግዥው ወይም ከማሰተላለፉ በፊት ለባለስልጣን መ/ቤቱ ማሳወቅ አለባቸው፡፡

ክፍል አምስት

                          የውህደት ዳሰሳ ደረጃዎች

 1. በተዋሀጆች የቀረቡ ማስታወቂያዎች ሙሉ ማስታወቂያዎች የሚባሉት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ ነው፡፡ ዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ መነሻ ቀንም የሚቆጠረው መረጃዎቹ ተጠቃለው ከቀረቡበት ቀን ጀምሮ ያለው ነው፡፡
 2. ዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ ወደ ደረጃ ሁለት የሚተላለፍ ከሆኑ ባለስልጣኑ ይህንኑ ውሳኔው ለአመልካቾች መግለጽ ይኖርበታል፡፡
 3. ባለስልጣኑ በአመልካቾች የቀረበው ማስታወቂያ ላይ ያለውን ምልከታ ከአመልካቾች በተጠየቀ ጊዜ ያሳውቃል፤ ውህደቱ በንግድ ውድድር፤ በገበያ እና በህዝብ ጥቅም ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ጎን በተመለከተ አመልካቾች ያላቸው ሌላ አማራጭ ካለ ይጠይቃል፡፡ የሚቀርበውን አማራጭም ያጠናል፡፡
 4. በውህደት ዳሰሳ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውህደቱ በውድድር ላይ ሊያደርስ የሚችለው አዎንታዊና አሉታዊ ውጤት፤ውህደቱ ሊፈጥር የሚችለው ውጤታማነት፤ውህደቱ በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያለው ውጤት፤ውህደቱ ሌሎች ተወዳዳሪነትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ውጤቶች ያሉት መሆኑ፤ውህደቱ የህዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑ የሚኖረው የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ ምን እንደሆነ በዝርዝርና በጥልቀት የሚመረመር ይሆናል፡፡

26 መካከለኛ ውህደት

መካከለኛ ውህደት በሁለት የዳሰሳ ጥናት ደረጃዎች ውስጥ ሊያልፍ ይችላል፡፡

           26.1. ደረጃ አንድ

 1. የውህደት ማስታወቂያዎችን በክፍል ሦስት የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸው ቅደመ ሁኔታዎች አሟልተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡
 2. መካከለኛ ውህደት ማስታወቂያ ተሟልቶ ከቀረበ በኃላ በ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ታይቶ ውሳኔ የሚያገኝ ይሆናል፡፡ይህ የጊዜ ገደብ እንደአስፈላጊነቱ ማስታወቂያ ለማስነገር የሚወስደውን ጊዜ አይጨምርም፡፡
 3. በዚህ ደረጃ ውስጥ ባለስልጣኑ ከባለጉዳዮችና ከሶስተኛ ወገን አንጻር በዉህደቱ ላይ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ውህደቱ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ የማይኖረው ከሆነ ውህደቱን ይፈቅዳል፡፡
 4. ውህደቱ በንግድ ውድድሩ፤ በህዝብ ጥቅም እና በገበያ ሁኔታ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ሁኔታ ተገልጾ በቅድመ ሁኔታ ለመፍቀድ የሚቻል ከሆነ እና ቅድመ ሁኔታውን ተወሀጆች የሚያሟሉ ከሆነ ውህደቱ ይፈቀዳል፡፡
 5. በዚህ ደረጃ ውስጥ ውሳኔ ለማስተላለፍ በቂ የሆነ መረጃ ካለ ወይም ተጨማሪ ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ የማያስፈለግ ከሆነ በዚሁ ደረጃ ውስጥ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡
 6. መካከለኛ የውህደት ማስታወቂያዎች ታይተው በ15 የስራ ቀናት ውሳኔ እንዳያገኙ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ካሉ እና ለዚህም ተጨማሪ መረጃዎችን የሚስፈልግ ከሆነ ጉዳዩ ወደ ደረጃ ሁለት በማስተላለፍ በባለስልጣን መ/ቤቱ በ15 ቀናት ይራዘማል፡፡
 7. መካከለኛ የውህደት ማመልከቻዎች በዚህ ደረጃ ላይ ታይተው ውሳኔ የማያገኘው፡፡

ሀ. ተጨማሪ ማስረጃ ካስፈለገ፤

ለ.  ከገበያ፣ ከውድድርና ከህዝብ ጥቅም አንፃር ዳሰሳ ሲካሄድ የተገኘው ግኝት ለቀረበው

ማስታወቂያ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ተጨማሪ ግዜና የውሳኔ ሃሳብ የሚያስፈልግ

መሆኑ ከታመነበት፤

ሐ. ሌሎች በውህደት ባለስልጣኑ እንደ አሳማኝ ምክንያቶች የሚታዩ ጉዳዮች ከቀረቡ ነው፡፡

26.2.  ደረጃ ሁለት

 1. በደረጃ አንድ መካከለኛ የውህደት ማስታወቂያዎች ታይተው ውሳኔ ለመስጠት የማይቻል ሲሆን እና ጥልቀት ያለው ዝርዝር ዳሰሳ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በዚህ ደረጃ የሚታይ ይሆናል፡፡
 2. በዚህ ደረጃ ዳይሬክቶሬቱ የሚዋሃዱ አካላትን በጉዳዩ ዙሪያ የበለጠ መረጃ እንዲያቀርቡ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 3. ወደዚህ ደረጃ የተላለፈው ጉዳይ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
 4. ከዚህ በላይ በተካሄደው ዳሰሳ ጥናት ዉህደቱ በንግድ ዉድድር ከህዝብ ጥቅም እና በገበያ ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ እንደማይኖረዉ ካመነበት ዉህደቱን ይፈቅዳል፣
 5. ዉህደቱ በንግድ ዉድድር ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረዉ ካመነበት ዉህደቱን ይከለክላል፣
 6. ዉህደቱ በንግድ ዉድደር ላይ ሊያስከትል የሚችለዉ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ የተወሰኑ ተያያዥ ግዴታዎች በማከል ዉህደቱን ሊፈቅድ ይችላል፡፡
 7. ውህደቱ ከሚያስከትለው የጎላ አሉታዊ ተጽኦኖ ይልቅ ከቴክኖሎጂ፤ ከአሰራር ቅልጥፍና ወይም ከሌላ ተወዳዳሪነትን ከሚያጠናክር ጠቀሜታ አንጻር የሚያስገኘው ጥቅም የሚያመዝንና ይህም ጠቀሜታ ውህደቱ ከተከለከለ በሌላ መንገድ ሊገኝ የማይችል ሲሆን ባለስልጣኑ ውህደቱን ይፈቅዳል፡፡

 

27 ትልልቅ ውህደት በተመለከተ

 • ደረጃ አንድ
 1. የውህደት ማስታወቂያ በክፍል ሦስት የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸው ቅደመ ሁኔታዎች አሟልተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡
 2. ትልልቅ የውህደት ማስታወቂያ ተሟልቶ ከቀረበ በኋላ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ ታይቶ ውሳኔ የሚያገኝ ይሆናል፡፡
 3. በዚህ ደረጃ ውስጥ ባለስልጣኑ ከባለጉዳዮችና ከሶስተኛ ወገን አንጻር በዉህደቱ ላይ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ውህደቱ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ የማይኖረው ከሆነ ውህደቱን ይፈቅዳል፡፡
 4. ውህደቱ በንግድ ውድድሩ፤ በህዝብ ጥቅም እና በገበያ ሁኔታ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ሁኔታ ተገልጾ በቅድመ ሁኔታ ለመፍቀድ የሚቻል ከሆነ እና ቅድመ ሁኔታውን ተወሀጆች የሚያሟሉ ከሆነ ውህደቱ ይፈቀዳል፡፡
 5. በዚህ ደረጃ ውስጥ ውሳኔ ለማስተላለፍ በቂ የሆነ መረጃ ካለ ወይም ተጨማሪ ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ የማያስፈለግ ከሆነ በዚሁ ደረጃ ውስጥ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡
 6. ትልልቅ የውህደት ማመልከቻዎች ታይተው በ30 የስራ ቀናት ውሳኔ እንዳያገኙ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ካሉ እና ለዚህም ተጨማሪ መረጃዎችን የሚስፈልግ ከሆነ ጉዳዩ ወደ ደረጃ ሁለት በማስተላለፍ ለ15 ቀናት ይራዘማል፡፡
 7. መካከለኛ የውህደት ማመልከቻዎች በዚህ ደረጃ ላይ ታይተው ውሳኔ የማያገኘው፡፡

ሀ.  ተጨማሪ ማስረጃ ካስፈለገ፤

ለ.  ከገበያ፣ ከውድድርና ከህዝብ ጥቅም አንፃር ዳሰሳ ሲካሄድ የተገኘው ግኝት ለቀረበው

ማስታወቂያ  ውሳኔ  ለመስጠት የሚያስችል በቂ ተጨማሪ ግዜና የውሳኔ  ሃሳብ

የሚያስፈልግ መሆኑ ከታመነበት፤

ሐ. ሌሎች በውህደት ባለስልጣኑ እንደ አሳማኝ ምክንያቶች የሚታዩ ጉዳዮች ከቀረቡ ነው፡፡

     27.2  ደረጃ ሁለት

 1. በደረጃ አንድ ትልልቅ የውህደት ማስታወቂያዎች ታይተው ውሳኔ ለማግኘት የማይቻል ሲሆን እና ጥልቀት ያለው ዝርዝር የዳሰሳ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በዚህ ደረጃ የሚጣይ ይሆናል፡፡
 2. በዚህ ደረጃ ዳይሬክቶሬቱ የሚዋሃዱ አካላትን በጉዳዩ ዙሪያ የበለጠ መረጃ እንዲያቀርቡ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 3. ወደዚህ ደረጃ የተላለፈው ጉዳይ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
 4. በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ዉህደቱ በንግድ ዉድድር፤በገበያ እና በህዝብ ጥቅም ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ እንደማይኖረዉ ካመነበት ዉህደቱን ይፈቅዳል፣
 5. ዉህደቱ በንግድ ዉድድር ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረዉ ካመነበት ዉህደቱን ይከለክላል፣ ወይም
 6. ዉህደቱ በንግድ ዉድደር ላይ ሊያስከትል የሚችለዉ የጎላ አሉታዊ ተፅእኖ የተወሰኑ ተያያዥ ግዴታዎች በማከል ዉህደቱን ሊፈቅድ ይችላል፡፡
 7. ውህደቱ ከሚያስከትለው የጎላ አሉታዊ ተጽኦኖ ይልቅ ከቴክኖሎጂ፤ ከአሰራር ቅልጥፍና ወይም ከሌላ ተወዳዳሪነትን ከሚያጠናክር ጠቀሜታ አንጻር የሚያስገኘው ጥቅም የሚያመዝንና ይህም ጠቀሜታ ውህደቱ ከተከለከለ በሌላ መንገድ ሊገኝ የማይችል ሲሆን ባለስልጣኑ ውህደቱን ይፈቅዳል

 

 

 

                               ክፍል ስድስት

            የውህደት ማስታወቂያ ዳሰሳ ጥናት ስለማድረግ እና ውሳኔ መስጠት

 • ቅድመ ውህደት ዳሰሳ ጥናት ስለማካሄድ
  • የቅድመ ውህደት ዳሰሳ ጥናት ከንግድ ውድድር ፤ከገበያ ሁኔታ እና ከህዝብ ጥቅም
  •  አንጻር ይካሄዳል፡፡

የቅድመ ውህደት ዳሰሳ ጥናት ከንግድ ውድድር አንጻር ሲካሄድ የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡

ሀ. በገበያ ውስጥ ያለው የገበያ ተዋናይ መጠን

ለ. ገበያውን በበላይነት ለመያዝ ያላቸው/የሚኖራቸው አቅም

ሐ. በተመሣሣይ የንግድ መስክ ገበያ ውስጥ ለመግባት የሚኖረው መሰናክል እና በገበያ ውስጥ

ያሉትን ተወዳዳሪዎች ከገበያ ውጭ የማድረግ አቅም

መ. ምርቱን የሚተኩ የንግድ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች በገበያ ውስጥ ያላቸው ድርሻ

ወይም መጠን፣

ሠ. የውህደት ድርጊቱን የሚፈጸምበት የንግድ ስራ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ እቃዎች ወደ

አገር በመግባት በኩል ያለው ደረጃ

ረ. በገበያው ውስጥ ያለው እድገት፣ ፈጠራ፣ ዋጋ እና ተፈጥሯዊ ባህሪ

ሰ. በገበያው ውስጥ ያሉ አቅራቢዎችን አና ሸማቾችን በማወክ በኩል ያለዉ ደረጃ እና

በአቅራቢዎች፣አከፋፋዮች እና ቸርቻሪዎች የመደራደር አቅም ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር

መሆኑ፣

ሸ. ሌሎች ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ጉዳዮች ላይ የዳሰሳ ጥናቱን መደረግ ይኖርበታል፡፡

 • የቅድመ ውህደት ዳሰሳ ጥናት ከገበያ አንጻር ሲካሄድ የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡

ሀ. አግባብነት ያለው የገበያ ሁኔታ ትንተና

ለ. የምርት/አገልግሎት አቅርቦትና ፍላጎት ሁኔታ፡-

ሐ. የምርት/አገልግሎት ዋጋ፣ የጥራት ደረጃ፣

መ. የግብዓት ሁኔታ፣

ሠ. የምርት/አገልግሎት ስርጭት መስመር ሁኔታ፣

ረ. የገበያ ድርሻ

ሰ. አግባብነት ያለው የገበያ ክልል ውስጥ ያለው ስብስብ ወይም ክምችት

ሸ. ሌሎች ከዚህ ጋር ተያያዝነት ያላቸዉ ጉዳዮች ላይ የዳሰሳ ጥናቱን መደረግ ይኖርበታል፡፡

 • የቅድመ ውህደት ዳሰሳ ጥናት ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ሲታይ የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡

ሀ. ውህደቱ ቢፈፀም የንግድ ዉድድሩን በመገደብ በህብረተሰቡ ላይ ከሚያደርሰዉ ተጽዕኖ

ይልቅ ጠቀሜታዉ የሚያመዝን ሆኖ መገኘት አለመገኘቱን ፣

ለ. ውህደቱ ቢፈፀም የኢኮኖሚ ልማትን  በማፋጠን ወይም ቴክኒካል እውቀትን በማስተላለፍ

ወይም የንግድ ዕቃዎችን አመራረትና ስርጭትን ወይም የአገልግሎት አቅርቦትን በማሻሻል

በኩል የጎላ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ስለመሆን አለመሆኑ፤

 1. ውህደቱ የሚፈፀመዉ በመክሰር ላይ ያለ የንግድ ድርጅትን በመታደግ በኩል ያለዉ ድርሻ የጎላ ስለመሆን አለመሆኑ፡
 2. ውህደቱ ቢፈፀም በአገሪቱ በአነስተኛና ጥቃቃን ወይም በማይክሮ ወይም በአነስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ደረጃ የተቋቋሙትን ወይም የተሰማሩትን ነጋዴዎች ብቁ ወይም ተወዳዳሪ ሆኖ እዲገኙ ለማደረግ የሚረዳ ስለመሆን አለመሆኑ/የሚችሉበትን እድል የሚፈጥሩ ስለመሆን አለመሆኑ፡፣
 3. ሌሎች ከቴክኖሎጂ ወይም ከብቃት ወይም ከተወዳዳሪነት አንፃር ጠቀሚታ ያላቸዉን ጉዳዮች
 4. 29. የውህደት ማስታወቂያ ተቃውሞ
 • ባለስልጣኑ በተዋሀጆች የቀረበውን ማስታወቂያ የተማላ መሆኑን ማጣራት ካካሄደ በኋላ እንዳስፈላጊነቱ የተቃውሞ ጥሪ ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣ በሚታተም ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ተቃውሞ ያለው አካል በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሁፍ በማድረግ በአመልካቹ በራሱ ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 • ባለስልጣኑ የሚያወጣው የተቃውሞ ማስታወቂያ ቀን፤ የአመልካቾች ስምና አድራሻ፤ ያመለከቱበት የውህደቱ ሁኔታ፤ የአመልካቾች የንግድ ስራ ቦታ፤ በምን ያህል ቀናት ተቃውሞ ማቅረብ እንደሚቻል፤ የባለስልጣኑ ስም እና ተቃውሞ የሚቀርብበት ቦታ እና ሌሎች ጉዳዮችን የያዘ መሆን አለበት፡፡
 • የውህደት ዳይሬክቶሬት የተቃውሞ ማመልከቻ ካጣራ በኃላ የውሳኔ ሀሳቡን ለዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተርም የውሳኔ ሀሳቡን ለዋና ዳይሬክተሩ በአጭር ግዜ ውስጥ ያቀርባል፡፡ዋና ዳይሬክተሩም የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክቶ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
 • የውህደት ተቃውሞ ማስታወቂያ ወጪ በውህደቱ አመልካች ድርጅቶች የሚፈፀም ይሆናል፡፡
 1. የውህደት ማስታወቂያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስፈልገው ግዜ
 • መካከለኛ የውህደት ዓይነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስፈለገው ግዜ 15 ቀናት ይሆናል፡፡ አስፈላጊ ሲሆን ለተጨማሪ 10 ቀናት ሊራዘም ይችላል፡፡ግዜው ሊራዘም የሚችለው በባለስልጣኑ ሲፈቀድ ነው፡፡
 • ትልልቅ የውህደት ዓይነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስፈልገው ግዜ 30 ቀናት ይሆናል፡፡ አስፈላጊ ሲሆን ለተጨማሪ 15 ቀናት ሊራዘም ይችላል፡፡ ግዜው ሊራዘም የሚችለው በባለስልጣኑ ሲፈቀድ ነው፡፡            
 1. ከውደት ዳሰሳ ጥናት በሓላ ሊተላለፉ የሚችሉ ውሳኔዎች ውህደቱን  መፍቀድ፤ መከልከል፤ ተያያዥ ግዴታዎችን በማስቀመጥ መፍቀድ፤ በልዩ ሁኔታ መፍቀድ ወይም የውህደት ፍቃድ መሰረዝ ሊሆን ይችላል፡፡
  • የሚተላለፉት ውሳኔዎች ይዘት የሚከተሉትን ሊይዝ ይችላል፤የአመልካቾች ስም፤የውሳኔው ርዕስ፤የማመልከቻው ይዘት፤የካፒታል መጠን፤የሼር ግብይት መጠን፤የውሳኔው ምክንያት፤የውሳኔው ማጠቃለያ፤የዋና ዳይሬክተሩ ወይም የተወካዩ ፊርማ ይሆናሉ፡፡

 

 1. ውሳኔ ማሳወቂያ ጊዜ
  • ባለስልጣኑ ውሳኔውን ከወሰነበት ግዜ ጅምሮ ወድያውኑ ለአመልካቾች ወይም ለህጋዊ

ወኪሎቻቸው በጽኁፍ ያሳውቃል፡፡

 • ከዚህ በላይ የተደነገገው አንቀጽ ቢኖርም ባለሰልጣኑ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎች እንዳስፈላጊነቱ በድረ-ገጽ ኢሜል፤ በፖስታ፤ በፋክስና በደብዳቤ ሊያስታውቅ ይችላል፡፡
  • ስለ ይግባኝ

ባለስልጣኑ ውህደትን በተመለከተ በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው አካል ውሳኔው በተሰጠ በ30 ቀናት ውስጥ ለፌደራል ንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡

 1. የውህደት ማስታወቂያ ስለማቋረጥ

የውህደት አመልካቾች ባለስልጣን መ/ቤቱ በውህደቱ ፈቃድ ጥያቄ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የውህደት ጥያቄው እንዲነሳ ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡

 • በዚህ መሰረት የሚቀርብ ጥያቄ በውህደት አመልካቾች በተናጠል ወይም በጋራ ሊቀርብ ይችላል፡፡
 • በአንቀጽ1መሰረት ከውህደት አመልካች አንደኛው ጥያቀውን ሲያቀርብ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለሌላኛው ውህደት አመልካች/ቾች ያሳውቃል፡፡
 • አመልካቾች የውህደት ጥያቄያቸውን አቅርበው ለተከታታይ 3 ወር በባለስልጣን መ/ቤቱ እንዲያሟሉ የተጠየቁትን መረጃዎች እና ማስረጃዎች ካላቀረቡ እንዲሁም በሌሎች ህጋዊ ምክንያቶች የውህደት ጥያቄው ሊቋረጥ ይችላል፡፡
 • በባለስልጣን መ/ቤቱ ወይም በአመልካቾች የተቋረጠ ማመልከቻ በድጋሚ  የውህደት ጥያቄ ማቅረብን የሚከለክል አይሆንም፡፡
 • የውህደት ማመልከቻው የተቋረጠው የውህደት ተጽእኖ  ዳሰሳ ጥናት በተደረገበ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ከሆነ እና ማመልከቻው በድጋሚ ከቀረበ በቀድሞው ጥናት መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ድጋሚ  የውህደት ተጽእኖ  ዳሰሳ ጥናት ማድረግን አይከለክልም፡፡

ክፍል ሰባት

ድህረ ውህደት ዳሰሳዊ ጥናት እና ክትትል

 1. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው የውህደት ፈቃድ መነሻ ተገቢ ቅድመ ሁኔታዎች ስለመፈጸማቸው ለመከታተል፤ ከውህደቱ ጋር ተያይዞ ጥቆማ ሲደርሰው እንዲሁም በራሱ ተነሳሽነት የድህረ ውህደት ዳሰሳዊ ጥናትና ክትትል ሊያደርግ ይችላል፡፡
 2. የውህደት አመልካቾች የውህደት ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ በገበያ ላይ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥር ስለመሆኑ መረጃ ከተገኘ በአዋጁ አንቀጽ 36 መሰረት በምርመራ እንዲጣራ ለሚመለከተው ክፍል ውጤቱ እና መረጃ ይላካል፡፡

ክፍል ስምንት

እርምጃ ስለ መውሰድ

 1. ባለስልጣን መ/ቤቱ ድህረ ውህደት ክትትል ወቅት የውህደት ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች፡
  • የውህደት ፈቃድ ያገኘው በሀሰተኛ ወይም በተሳሳተ እና የተጭበረበረ ማስረጃ መሆኑ ሲረጋገጥ፤
  • ውህደቱ የተፈቀደው በቅድመ ሁኔታዎች ሆኖ ቅድመ ሁኔታዎቹን ያለመሟላቱ ሲያረጋገጥ የውህደት ፈቃዱን በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ሊሰርዝ ይችላል፡፡
 2. ባለስልጣን መ/ቤቱ ከላይ በአንቀጽ 38(1 እና 2፣3) መሰረት የወሰደውን እርምጃ ለሚመለከታቸው መ/ቤቶች ማሳወቅ እና ተፈጻሚነታቸውን መከታተል አለበት፡፡

ክፍል ዘጠኝ

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

 1. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች

ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በባለስልጣኑ የተሰጡ የውህደት ፈቃዶች በዚህ መመሪያ የተሰጠ ተደርጎ የጸና ይሆናል፡፡ ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በመታየት ላይ ያሉ የውህደት ማስታወቂያዎች  በዚህ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

 1. ስለማሻሻል

የዚህ መመሪያ አውጪው አካል አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው መመሪያ ሊያሻሽል ይችላል፡፡

 1. መመሪያው ስለሚጻናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከ ……ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አቶ ያዕቆብ ያላ

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር

 

 

 

 

አባሪዎች  እና ቅጻ ቅጾች

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Pre-Acquisition notification form for buyer/seller Company applicants 001

 1. Name of the requesting enterprise/company፡ —————————————
 2. Address of the applicant enterprise/company:
  • Name of the country in which the enterprise/company is operating—————
  • City/State—————-Sub-city/ street ——————

E-mail ———————–Telephone no —————

 1. Request details of applicant enterprise/company:
  • Types of the sector the enterprise /company is engaged in፡

Agriculture                   industry             service

 • Types of goods or services being produced by the enterprise/company

——————————————————–

 • The enterprise’s/company’s amount of current capital in Birr:———————–
 • Name of the enterprise’s/companies from which the applicant wants to purchase/sell share or security: —————————-
 • Amount of share/security the applicant or individual shall purchase/selling Birr ——-
 1. Is the applicant enterprise/company currently producing? Yes no
 2. Other description (optional) ———————————————————————————-

 

I assure in my signature that the information I have provided above is correct.

Name and signature of the owner/manager who filled the information:

Name: ——————————————

Position: —————————————

Signature: —————————- Date: ————————–

For legal representative of the organization

Name and signature of the legal representative who filled the information:

Name: ——————————————

Position: —————————————

Address: Country: ————————City/State———— Sub City/Street————– Email Address: —————————– Phone no. ———————-

Signature: —————————- Date: ————————–

 

 

Pre-Acquisition Notification Form for Individual Applicants

 1. Name of the applicant: ———————————-
  • Address of the applicant:-
  • Nationality : —————————-
  • Name of the country the applicant is living /working in:———————-

Town/City: ——————————–

 1. Name of region/state where the applicant received his/her Identity card : ——————
 2. Name of the company/organization from which the applicant wants to purchase/sell share or security: —————————-
  • Address of the company:  Country: ———— City/State———— Sub City/Street—— Email Address: —————————– Fax no. ———————-
 3. Amount of share/security the applicant or individual shall purchase/sell in USD —————— or in Birr ———————————–
 4. Does the applicant have his/her own business organizations? Yes                     NO

IF YES,

 • Location of the business organization: Country  —————-   City/State —————Sub City / Street —–
 • Types of goods or services the organization is currently producing: —————————————————————————————————————
 • Types of input used to produce the above production: ————————————————————————————————————————————
 1. Total amount of capital or sales volume per year—————————————————–
 2. If there is additional information: ————————————————————————

I assure in my signature that the information I have provided above is correct.

Name and signature of the owner/manager who filled the information:

Name: ——————————————

Signature: —————————- date: ————————–

For legal representative of the applicant

Name: ——————————————

Address: Country: ————————City/State———— Sub City/Street——————— Email Address: ——————–Phone no. ———————-

Signature: —————————- Date: ————————–

 

Pre-merger notification form 003

(To be filled by applicant enterprises/company independently)

 1. Name of the requesting enterprise/company፡ —————————————
  • Address of the applicant enterprise/company:
  • Name of the country in which the enterprise/company is operating—————
  • City/State—————-Sub-city/ street ——————

E-mail ———————–Telephone no —————

 • Request details of applicant enterprise/company:
  • Types of the sector the enterprise /company is engaged in፡

Agriculture                   industry             service

 • Types of goods or services being produced by the enterprise/company

——————————————————–

 • The enterprise’s/company’s amount of current capital in Birr:———————–
 • Types of merger the applicant organization wants to undertake:
  • Partial merger (transfer of share and security)
  • full merger or acquisition
 • Types of organization of the proposed merger (after merger is undertaken)
  • Private limited company
  • Share company
  • Joint Venture
  • Ordinary Joint Venture
  • General partnership
  • Limited Partnership
 • Amount of capital of the proposed merger (amount of capital after merger is undertaken)in Birr ———————–
 • If the enterprise/company is partially merged with the other company/s, what will be its total contribution in Birr———————-
 • Lists of the enterprises/companies to be merged with the applicant enterprise/company

 

no Name of the company Types of sector the company is operating Types of goods or services produced Other

 

 • Is the applicant enterprise/company currently producing? Yes no
 • Other description (optional) ———————————————————————————————————————–

I assure in my signature that the information I have provided above is correct.

Name and signature of the owner/manager who filled the information:

Name: ——————————————

Position: —————————————

Signature: —————————- Date: ————————–

 

For legal representative of the organization

Name and signature of the legal representative who filled the information:

Name: ——————————————

Position: —————————————

Address: Country: ————————City/State———— Sub City/Street————– Email Address: —————————– Phone no. ———————-

Signature: —————————- Date: ————————–

 

 

 

በገበያ ውስጥ የአቅራቢዎች ስብስብ መጠን ለመለካትም Herfindahl-Hirschman Index (HHI) እና concentration ratios (CR(n)) ዘዴዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆኑ፡

 

የ Herfindahl-Hirschman Index (HHI) ውጤት 15 %  እና ከዚያ በታች ከሆነ የገበያ ስብስብ  የሌለ መሆኑን  ፣ ከ15% -25%  ከሆነ መካከለኛ የገበያ ስብስብ ፣ ከ 25% በላይ ከሆነ ከፍተኛ የገበያ ስብስብ እንዲሁም

Formula for calculating market concentration

 

Where si is the market share of firm i in the market and N is the number of firms.

Herfindahl-Hirschman Index is the sum of the squres of the market shares of each firm in the industry. We can’t get a bigger HHI number than 10,000.  Every monopoly would have an HHI of 10,000.

Example: find the HHI in an Industry with just two firms each firm has 50 percent of the market share. Thus, in a market with two firms that each have 50 percent market share, the Herfindahl index equals 0.502+0.502 = 1/2.

HHI = 502+502= 2,500 + 2,500 = 5,000

               OR 0.502+0.502= 0.25 + 0.25 = 0.50

Highly competitive index- if   HHI index below 0.01 (or 100)

Unconcentrated indexif HHI index below 0.15 (or 1,500)

Moderate concentrationif HHI index between 0.15 to 0.25 (or 1,500 to 2,500)

High concentrationif HHI index above 0.25 (above 2,500) indicates

Threfore, asHHI decreases level of market concentration also decline

 

 

 

 

 

 

 

የአቅራቢዎች የገበያ ስብስብ መጠን /Concentration Ratios/

የ Concentration Ratios ውጤት በሚመለከት ደግሞ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው አራት አቅራቢዎች የገበያ ክምችት (CR4 ) እና በገበያው ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው ስምንት አቅራቢዎች የገበያ ክምችት (CR8) የገበያ ስበስብ መጠን መሰረት በማድረግ CR 100% ከሆነ ገበያው ውስጥ አንድ አቅራቢ ብቻ ያለ መሆኑንና በብቸኝነት (በሞኖፖል) መያዙን፣ CR ከ 80% እስከ 100% ሲሆን ከፍተኛ ገበያ ስብስብ ያለ መሆኑንና ገበያው በጥቂቶች መያዙን ጠቋሚ ሲሆን እስከ 50% ድርስ ደግሞ ገበያው ዝቅተኛ ክምችት ወይም ስብስብ ያለበትና አንጻራዊ ውድድር የሚስተዋልበት መሆኑን ያሳያል፡፡ ገበያው 0% የክምችት ወይም ስብስብ መጠን (Concentration ratio) ካለው ፍጹም የሆነ ውድድር ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡

How to calculate Concentration Ratios

Two common ratios:

 1. The Four-Firm Concentration Ratio measures the totalmarket shareof the four largest firms in an industry.
 2. The Eight-Firm Concentration Ratio measures the total market share of the eight largest firms in an industry.

The concentration ratio is the percentage of market share held by the largest firms (m) in an industry.

CRm= Σmi=1 si

Therefore it can be expressed as:    CRm = s1 + s2 +…. + sm. Where si is the market share and m defines the ith firm.

Concentration ratio levels:

Concentration ratios range from 0 to 100 percent. The levels reach from no, low or medium to high to “total”concentration.
No concentration: 0% means perfect competition or at the very least monopolistic competition. If for example CR4=0 %, the four largest firm in the industry would not have any significant market share.

Total concentration: 100% means an extremely concentrated oligopoly. If for example CR1= 100%, there is a monopoly.

Low concentration: 0% to 50%. This category ranges from perfect competition to oligopoly.

Medium concentration:  ranges from 50% to 80%

High concentration: rangesfrom80% to 100%.

 

You must be to post a comment